ጉብኝት

መምህር አብዱ ለየት ያለ ልምድ እንድንቀስም ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ይዘውን ተጉዘዋል፡፡ ዘጠኙንም ክልሎች እንድናይ በማሰብም ሁለት ሁለት እያደረጉ ነበር የወሰዱን እናም በተቻለ መጠን የየክልሉን ገፅታ በሲቪክስ ክፍለ ጊዜ ለጓደኞቻችን ለማሳየት  እንድንችል በዶክመንተሪ መልክ ቀርፀነዋል፡፡ የተለያዩትን የብሔር ብሔረሰቦች ባህል እንዲሁም ቅርሶቻቸውን ማየት በጣም የሚያስደስት ሆኖ ነው ያገኘነው፡፡ እዚህ ውስጥ ብዙ ነገር ነው ያለው!በጉብኝታችን ወቅት ያነሳናቸው አንዳንድ ፎቶዎችም አሉ፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ሊታዩ የሚችሉ ቅርሶች ቢኖሯቸውም ለማንሳት የቻልነውንና በትንሹ ስለ ባህሉ ያስረዳል ብለን ያሰብነውን ከየክልሉ እንደ ባህላዊ ጭፈራና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የመሳሰሉትን ይዘናል፡፡ እናንተም ለወደፊት ለመጎብኘት ትፈልጉ ይሆናል፡፡ በጣም ደስ ይለናል!!