ዝርዝር

ኩረጃ

ነገ ለምንፈተነው ፈተና ኪያ ዝግጁ አይደለም!! በመጀመሪያ አበበን ከዚያም ያሬድን እንዲያስኮርጁት ሲያግባባቸው ነበር፡፡ እኔና የኔ ወንድም አበበ ማጥናት እንዳለበት ነግረነዋል፡፡ ከኛ ምንም እንደማያገኝ ሲገባው ከስነ ዜጋ አስተማሪያችን ቢሮ መልስ ለመስረቅ ሄደ፡፡ የስነ ዜጋ መምህርት ሊኮርጅ ሲል ያዙት፡፡ ልናሳምነው በጣም ሞከርን በመጨረሻም በሰራው  ስራ ተፀፀቶ ሁላችንንም  ይቅርታ ጠየቀን፡፡በደንብ አጥንቶ ስለነበር ከአንድ ወር በኋላ የተፈተንነውን ፈተና ጥሩ ውጤት አመጣ፡፡ ኩረጃ የጀብደኝነት ምልክት ሳይሆን ራስን የማታለያ ዘዴ ነው፡፡ አንድ ሰው ለኩረጃ የሚያጠፋውን ጊዜ ለጥናት ቢጠቀምበት ጥሩ ውጤት ሊያገኝበት ይችላል፡፡     

Back