ተዋንያን

እኛ ልጆች

ዋነኞቹ ገፀ ባህሪያት እኛ ነን። እናም በታሪኩ ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ታገኙናላችሁ! ሁላችንም ጓደኛሞች ነን ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ላንግባባ እንችላለን። አለመግባባታችን ችግር የለውም፤ ምክንያቱም ይህ የተለመደ ሂደት ነው!...

ኡጁሉ

ከቡድናችን ትልቁ ኡጁሉ ሲሆን ግልፅ ቅን፣ጥሩ አሳቢ እና ገራገር ሲሆን ቁመቱ በጣም ረጅም ነው! ከተፈጥሮ ጋር ቁርኝት ያለው የጋምቤላ ተወላጅ ነው፡፡ ምክንያታዊ ከመሆኑም በተጨማሪ ለማንኛውም አጣብቂኞች ወይም ችግሮች መፍትሄ ይዞ...

ኪያ

ኪያ ሁልጊዜ የበላይነት የሚሰማው እንደውም አንዳንዴ ጋጠወጥ የሚባል ባህርይ ያለው ልጅ ነው፡፡ በሁሉም ነገር ከሌሎቻችን የበለጠ መስሎ ቢሰማውም እውነታው ግን ከሌሎቻችን እኩል ነው፡፡ በስፖርት በጣም ጎበዝ ቢሆንም በትምህርቱ ግን ሰነፍ...

ሸዊት

ሸዊት ከቡድናችን ትንሿ ናት፡፡ የመጣችው ከገጠር ሲሆን የምትኖረውም ከአክስቷ ጋር በሆቴላቸው ውስጥ ነው፡፡ እኔና ሸዊትን እንዲሁም ሌሎች የቅርብ ጓደኞቻችንን አንድ የሚያደርገን ለአትክልት ያለን ፍቅር ነው፡፡ ችግር ሲደርስባት...

ያሬድ

ያሬድ የክፍላችን ቀልደኛ ነው። በጣም ያስቀናል። አንዳንድ ጊዜ ግን ስርዓት የለሽ ስለሚሆን ችግር ላይ ይወድቃል። የሲቪክስ አስተማሪያችን መምህርት መላክነሽ ክፍል ውስጥ እንዳይመገብ ሁሉ ጊዜ ትቆጣዋለች። የሂሳብና የኮምውፒተር ትምህርቶች...

አበበ

የኔ ወንድም አበበ ከእኔ ጋር በጥቂቱ ይመሳሰላል። ልክ ስሙ በርዕሱ ላይ እንደመኖሩ! እኔና እርሱ በህብረት ከጓደኞቻችን ጋር ህገ መንግስትን በጉዟችን እናንፀባርቃለን፡፡ አበበ የስዕል ችሎታውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ...

አበባ

እኔ! አበባ! አንዳንድ ሰዎች የትዕይንቱ ኮከብ ነች ይሉኛል። እውነታው ግን እኔ ልክ እንደ ሌሎቹ ልጆች ነኝ፡፡ በርግጥ ችግሮችን መፍታት ያስደስተኛል። እናም የኛ የልጆችን መብቶች ለማወቅ የህገመንግስት መፅሐፍ በየጊዜው...