ዝርዝር

አኒሜሽን በኢትዮጵያ

በድሮ ዘመን ኢትዮጵያዊ ቅድም አያቶቻችን በተለያዩ ደረጃ ሂደታዊ ለውጦችን የሚያሳዩ ስዕሎችን በተለይም በአብያተ ክርስቲያናት ያሉ ገድሎችን በተለያየ መልኩ ይስሎ ነበረ ነገር ግን እነኚህ ስዕሎች ወደ እንቅስቃሴ ተቀይረው ልዩ ልዩ ነገሮችን ሲያካሂዱ ለማየት እምብዛም አልታደሉም ነበር። በኢትዮጵያ እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ተረቶች እንደመገኘታቸው ምንም አይነት የአኒሜሽንም ሆነ የልጆች መፅሐፍት እትም ለህብረተሰቡ የማቅረብ ባህል ሳይንሰራፋ ለዘመናት ቆይቷል ነገር ግን ሌሎች እንደነ ዲዝኒ ድሪም፤ ዎርክስ ወዘተ የሰሩትን ታላቅ የአኒሜሽን ስነ ጥበብ ታሪክ በኢትዮጵያም ለመድገም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀደምት ስፍራውን የያዘ ሲሆን በዚህም የተነሳ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሬድዮና የቴሌቪዥን ድርጅት የመጀመሪያውን የአኒሜሽን ፊልም አየር ላይ ለማዋል ችሏል።

ይህም እንቅስቃሴ በሃገሪቷ ለልጆች ፕሮግራም የነበረውን አነስተኛ ትኩረት ወደተሻለ ደረጃ እንደሚያደርሰው ጥርጣሬ የለንም።