“አበባ እና አበበ” በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የመጀመሪያው አኒሜሽን ፊልም ነው፡፡ ይህ በልጆች ፊልም ፎርማት 51x7 ደቂቃ የሆነና (በሳምንት አንድ ጊዜ ለአንድ አመት) ደረጃውን ጠብቆ የተሰራ ፊልም የተሰራ ከ6-12 ዓመት ላሉ ህፃናት ሲሆን እንደመነሻ የኢትዮጵያን ህገመንግስት አድርጎ ህፃናትን ስለመብቶቻቸው እያስተማረ የሚያዝናና ፊልም ነው፡፡